በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊኒ ቢሳው በሁለት የመንግስት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ


ከፓርላማ ፊት ለፊት ያለው እና ለወትሮ ሥራ የበዛበት ጎዳና ፀጥ እረጭ ብሎ ይታያል ጊኒ ቢሳው
ከፓርላማ ፊት ለፊት ያለው እና ለወትሮ ሥራ የበዛበት ጎዳና ፀጥ እረጭ ብሎ ይታያል ጊኒ ቢሳው

በጊኒ ቢሳዉ በብሔራዊ ዘቡ እና በፕሬዝደንታዊ ጥበቃ ልዩ ኃይሉ መካከል በመዲናዋ ቢሳዉ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ተከተሎ፣ የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ነገሮችን በቁጥጥር ሥር ማድረጉን አስታውቋል።

ትናንት ሌሊት እና ዛሬ ጠዋትም በመዲናዋ የትኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ያለመረጋጋት በሚስተዋልባት ትንሿ የምዕራብ አፍሪካ አገር ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ያመለከተ ነው ተብሏል።

የብሔራዊ ዘቡ አዛዥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው አልያም እጅ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የተኩስ ልውውጡ መቆሙንና፣ ፀጥታ መስፈኑን ሠራዊቱ አስታውቋል። ሠራዊቱ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ፎቶ፣ የበብሔራዊ ዘቡ አዛዥ ደም በነካው ልብሳቸው ሆነው በግልጽ መኪና ላይ ተጭነው ተስተውለዋል። የበብሔራዊ ዘቡ አባላት፣ ሁለት የታሠሩ የመንግስት ባለሥልጣናትን ለማስለቀቀ በሚል፣ የፖሊስ ሕንፃዎችን ሲወሩና ባለሥልጣናቱን ይዘው ሲሄዱ የተኩስ ልውጡ እንደተከሰተ ታውቋል።

ሁለቱ ባለሥልታናት በኋላ ላይ መገኘታቸውን ሠራዊቱ አስታውቋል።

ፕሬዝደንቱ በሚገኙበት አካባቢ ያሉ ሕንፃዎች ጥበቃው መጠናከሩ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG