በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቃላሚኖ የሮቦቲክስ ፈጠራ አሸናፊዎች እስከ “ኅዋ ምርምር የመጠቀ” ተምኔት


 የቃላሚኖ የሮቦቲክስ ፈጠራ አሸናፊዎች እስከ “ኅዋ ምርምር የመጠቀ” ተምኔት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:22 0:00

የቃላሚኖ የሮቦቲክስ ፈጠራ አሸናፊዎች እስከ “ኅዋ ምርምር የመጠቀ” ተምኔት

የትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀው፣ ስምንተኛው ዙር አገር አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከላት ውድድር፣ ባጋመስነው የኅዳር ወር መጀመሪያ ሳምንት፣ በዐዲስ አበባ ሲካሔድ፣ በመቐለ የቃላሚኖ ልዩ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቡድን አሸናፊዎች ኾነዋል፡፡

ተማሪዎቹ፣ በጦርነት ምክንያት ከትምህርት ርቀው ቢቆዩም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ባደረጉት ዝግጅት ለአሸናፊነት እንደበቁ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም፣ ጠንክረው ተምረውና ሠርተው፣ በሮቦቶች በሚከናወን የኅዋ ሳይንስ ምርምር ውስጥ የመሳተፍና ማኅበረሰቡ በቅናሽ ዋጋ ችግሮቹን ለማቃለል የሚችልባቸውን ፈጠራዎችን የማበርከት ተምኔት እንዳላቸው ያመላከቱትን የቡድኑን አባላት፣ የአሜሪካ ድምፅ አነጋግሯቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG