በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማይናማር ታጣቂ ቡድን ከቻይና ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ተቆጣጠረ


በማይናማር እና ቻይና ድንበር አቅራቢያ ከሚቃጠል አንድ የጭነት መኪና የሚወጣ ጭስ አካባቢውን ሽፍኖት ይታያል
በማይናማር እና ቻይና ድንበር አቅራቢያ ከሚቃጠል አንድ የጭነት መኪና የሚወጣ ጭስ አካባቢውን ሽፍኖት ይታያል

በማይናማር የሚገኝ አናሳ ጎሳ ታጣቂ ቡድን ወደ ቻይና የሚያቋርጠውን ቁልፍ ድምበር ከገዢው የጁንታ መንግስት ወስዶ መቆጣጠሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች እና አንድ የጸጥታ አባል አስታወቁ።

ሦስት አናሳ ብሄሮች የፈጠሩት ጥምረት፣ በጥቅምት ወር የሀገሪቱ ጦር ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ ወዲህ፣ በቻይና ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የማይናማር ሰሜናዊ ግዛት ግጭቶች ተባብሰዋል።

ጥምረቱ ከቻይና ጋር ለሚደረገው የንግድ ልውውጥ ቁልፍ የሆነ ከተማ እና ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደራዊ ቦታዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ለገጠመው ጁንታ የንግድ መተላለፊያ መንገዶችን እያሳጡ ይገኛል።

ከሦስቱ የጥምረቱ አባላት አንዱ የሆነው የማይናማር ብሄራዊ ዲሞክራቲክ ጥምረት ጦር ባካሄደው ጥቃት ኪን ሳን ካያውት የተሰኘውን ድንበር መቆጣጠሩን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን፣ ወደ ቻይና የሚያስተላልፈው ይህ ድንበር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግቶ ቆይቶ እ.አ.አ በ2022 ከተከፈተ ወዲህ በማይናማር እና በቻይና መካከል ዋና የንግድ መተላለፊያ ስፍራ ሆኖ ቆይቷል።

በዋናነትም ማሽኖች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የእርሻ ትራክተሮች እና ሌሎች ሽቀጣሸቀጦች በዚህ ድምበር እንደሚተላለፉ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG