በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስተኛ ዙር ታጋቾች ዛሬ ይለቀቃሉ


የእስራኤል ጦር ይፋ ባደረገው በዚህ ፎቶ፣ ሂላ ቶተም ሾሻኒ የተባለች ታጋች ተለቃ እስራኤል ውስጥ ከአጎቷ ጋር ስትገናኝ ያሳያል
የእስራኤል ጦር ይፋ ባደረገው በዚህ ፎቶ፣ ሂላ ቶተም ሾሻኒ የተባለች ታጋች ተለቃ እስራኤል ውስጥ ከአጎቷ ጋር ስትገናኝ ያሳያል

እስራኤል እሁድ እለት በሐማስ የሚለቀቁ ታጋቾች ስም ዝርዝር እንደደረሳት አስታውቃለች። ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ከጋዛ ነፃ ከሚወጡት ታጋቾች መኻከል አንድ አሜሪካዊ ሊገኝበት እንደሚችል ገልጻለች።

የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ የሚያካሒዱትን የውጊያ ጥቃት ለአራት ቀናት ለማቆም የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ እሁድ እለት ታጋኞች የሚለቀቁት ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የተኩስ ማቆምም ስምምነቱ ማክሰኞ ይጠናቀቃል።

የዋይት ኃውስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን፣ ኤን ቢ ሲ በተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ከሚተላለፈው 'ሚት ዘ ፕሬስ' ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ቢያንስ አንድ አሜሪካዊ ታጋች እሁድ ትለቃለች ባላ የምታምንበት ምክንያት አላት ብለዋል።

"የአራት አመቷ አቢጌል ኤዳን እንደምትለቀቅ ተስፋ እንዳደርጋለን፣ ነገር ግን ሆኖ እስክናየው ድረስ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም"።

ምን ያክል አሜሪካውያን በሐማስ ታግተው እንደሚገኙ እስካሁን ባይታወቅም፣ ሱሊቫን ቀደም ሲል ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዘጠኝ አሜሪካውያን እና አንድ በአሜሪካ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የውጭ ዜጋ በሐማስ ተይዘዋል ብላ እንደምታምን ተናግረው ነበር።

የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣናት ዛሬ የሚለቀቁትን ታጋቾችን ስም ዝርዝር እያጣራ ሲሆን የታጋቾቹ ቤተሰቦች እንዲያውቁ መደረጉንም መንግስት አስታውቋል።

ሐማስ ቅዳሜ ረፋድ ላይ 17 ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን፤ 13ቱ እስራኤላውያን፣ አራቱ ደግሞ የታይላንድ ዜግነት ያላቸው ናቸው። የታጋቾቹን መለቀቅ ተከትሎ እስራኤልም 39 ፍልስጤማዊ እስረኞችን ለቃለች።

አንድ በሐማስ ይፋ የተደረገ ቪዲዮ እንደሚያሳየው ታጋቾቹ የመንቀጥቀጥ ምልክት ቢኖርባቸውም፣ በአብዛኛው ግን በጥሩ አካላዊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እና ጭንብል ያጠለቁ ታጣቂዎች ከጋዛ ይዟቸው ወደሚወጣው የቀይ መስቀል መኪናዎች እንደመሯቸው አሳይቷል። እስራኤል ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኃላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እሁድ ባወጣው መግለጫ፣ የእስራኤል ወታደሮች ትላንት ምሽት ዌስት ባንክ ውስጥ ቢያንስ ስድስት ፍልስጤማውያንን በጥይት ተኩሰው ገድለዋል ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG