በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ጋዜጠኞች እና አራት የፍልስጤም ታጣቂዎች ሊባኖስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ ተገደሉ

ሁለት ጋዜጠኞች እና አራት የፍልስጤም ታጣቂዎች ሊባኖስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ ተገደሉ
ሁለት ጋዜጠኞች እና አራት የፍልስጤም ታጣቂዎች ሊባኖስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ ተገደሉ
እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ያደረገችው የአየር ድብደባ፡ ሁለት ጋዜጠኞቹን መግደሉን ዋና ቢሮውን በቤይሩት ያደረገው የመላው አረብ የቴሌቭዥን ጣቢያ አስታወቀ።
አል-ማያዲን የተባለው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጨምሮ እንዳመለከተው፣ ፋራህ ኦማር የተባለ ዘጋቢ እና ራቢህ ማማሪ የተባለ የካሜራ ባለ ሞያ፣ ዛሬ ማክሰኞ ሊባኖስን ከእስራኤል ጋር ከሚያዋስነው ድምበር አካባቢ ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሲዘግቡ ነው የተገደሉት።.
የቴሌቭዥን ጣቢያው ከሊባኖሱ ታጣቂ ኃይል ሂዝቦላ ጋር ፖለቲካዊ አጋርነት ያለው ሲሆን፤ ሂዝቦላ በአጻፋው በሰሜናዊ እስራኤል የሚሳኤል ጥቃት መፈ’ጸሙን አመልክቷል።
በሌላ ዜና፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ባደረገችው ሌላ የአየር ድብደባ አራት የሃማስ አባላትን መገደላቸውን፣ አንድ የፍልስጤም ባለስልጣን እና አንድ የሊባኖስ የጸጥታ ባለስልጣን በተመሳሳይ ይፋ አድርገዋል። ከእስራኤል ጋር በመዋጋት ላይ የሚገኘው ሐማስ በርካታ ሚልሻዎቹ ሊባኖስ ውስጥም መኖራቸው ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG