ዛሬ እሁድ በመላው ኬኒያ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተክትሎ በተከሰተ የመሬት መናድ እና ጎርፍ በአስር ሺህዎች የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሞምባሳ ወደብ ላይ አገግሎት እንዲቋረጥ አድርጓል።
ባለፉት ሳምንታት ከኤልኒኖ የአየር ሁኔታ ክስተት ጋር ተያይዞ በአፍሪካ ቀንድ ድንገተኛ እና ከፍተኛ ዝናብ የተከሰተ ሲሆን፤ ዝናቡ በኬኒያ በትንሹ 46 የሚደርሱ አካባቢዎች ላይ የሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
የኬኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ባወጡት መግለጫ በኬንያ ቢያንስ 80,000 አባወራዎች ተጎድተዋል "በየቀኑ ቁጥሩ እየጨመረ" ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም መንግስት ሄሊኮፍተሮችን እና የድንገተኛ አገልግሎትን በመጠቀም ለተጎዱ ቤተሰቦች ድጋፍ በማድረግ እና የነፍስ አድን ስራዎችን በመስራት ላይ ነው ብለዋል።
በሀገሪቱ በደረሰው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ወደ ሞምባሳ ወደብ እና ወደ ናይሮቢ በሚወስደው የጭነት ባቡር መስመር ላይ "ያልተጠበቀ መዘግየት" የተከሰተ ሲሆን ይኸም የወደብ አገልግሎት እንዲስተጓጎል አድርጓል።
መድረክ / ፎረም