በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን 20 ሀገራት እና የአፍሪካ ጥምረት ስብሰባ ሊጀመር ነው


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ

ከ12 በላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቡድን 20 የአፍሪካ ጥምረት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጀርመን አቅንተዋል። ጥምረቱ በማደግ ላይ ያለችው አፍሪካን ከአውሮፓ ጋር በመዋዕለ ንዋይ ትስስር እንዲኖራት ለማድረግ ያለመ ነው።

የቡድን 20 ሀገራት የአፍሪካ ጥምረት አባልት ኢትዮጵያን ጨምሮ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሴኔጋል፣ ጊኒ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሩዋንዳ፣ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናቸው።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ላይ ያለውን አዲስ የአውሮፓ ፍላጎት ያረጋገጡት የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ዴር ሌየን ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት፣ በጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ አስተናጋጅነት በርሊን ላይ ከሚሳተፉ መሪዎች ማካከል እንደሚሆኑ የጀርመን መንግስት ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እ.ኤ.አ. በ2021 መገባደጃ ላይ ስልጣን ከያዙ በኋላ አፍሪካን በተደጋጋሚ የጎበኙት የጀርመኑ መርሄ መንግስት ሹልዝ በነገው ዕለት በበርሊን የጀርመን እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ከማዘጋጀታቸው በፊት ዛሬ ዕሁድ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ።

አውሮፓ እና ዩናይትድ ስቴትስ በከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ሁለተኛዋ በሆነችው አህጉር አፍሪካ ላይ ሩሲያ እና ቻይና በወሳኝ መዓድናት፣ በምጣኔ ሀብት ዕድሎች እና በጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖ ዙሪያ እየፈጠሩ ያሉትን ጫና ለመገዳደር በመጣር ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ. በ2017 በጀርመን በቡድን 20 ፕሬዝዳንትነት የተመሰረተው የአፍሪካ ትስስር የለውጥ አስተሳሰብ ያላቸውን የአፍሪካ ሀገራት፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የሁለትዮሽ አጋሮችን በማሰባሰብ የልማት አጀንዳዎችን በማስተባበር እና በኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ለመወያየት ያለመ ነው።

“አውሮፓ ስለ ኢንቨስትመንት ስታወራ፣ ቻይና ግን ያለ ምንም የሞራል ትምህርት ገንዘብ ትሰጣለች” ሲሉ የአፍሪካ አገሮች ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። ምንም እንኳን በአሁን ሰዓት ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠው ብድር እየቀነሰ ቢመጣም፤ አውሮፓ በአፍሪካ የምርት አቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማብዛት በመጣር ላይ ትገኛለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG