በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሐዲያ ዞን፣ መምህራን ለገጠማቸው ችግር፣ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ጠየቀ፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶር. ዮሐንስ በንቲ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ለወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው የዞኑ መምህራን አቤቱታ ማቅረባቸውንና ማኅበሩም አቤቱታቸውን ተቀብሎ፣ ለትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዳቀረበ ተናግረዋል፡፡
የደመወዝ መቋረጥ፣ የመምህራኑን ሕይወት ከማናጋት አልፎ፣ የትምህርት ሥርዐቱን ይጎዳዋል፤ ያሉት ዶር. ዮሐንስ፣ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚያሻው አሳስበዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም