በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት፣ ከዐርብ ጀምሮ ተፈፀመ በተባለ ጥቃት፣ ከአምስት በላይ ሰዎች እንደተገደሉ፣ ከአካባቢው እየሸሹ ወደ ኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የተፈናቀሉ የሟች ቤተሰቦች ተናገሩ።
ጥቃቱ፣ “በፋኖ ታጣቂዎች ነው የተፈጸመው” ሲሉ የገለጹት የዐይን እማኞቹ፣ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።
በቡሬ ወረዳ ያለውን የፋኖ አደረጃጀት እንደሚመሩ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት ሻለቃ ጌታሁን በሬ የተባሉ ግለሰብ፣ ድርጊቱን ኀይሎቻቸው እንዳልፈጸሙ ጠቅሰው ክሱን አስተባብለዋል፡፡ “ድርጊቱ በፖለቲከኞች የተቀነባበረና የብልጽግና ፓርቲ በአደራጃቸው ፋኖዎች የፈጸሙት ነው፤” ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከቡሬ ወረዳ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ኾነ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም