በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ ጦር እና በአማጺያን መካከል ኪዳል ግዛት ውስጥ ግጭት ተቀሰቀሰ


.
.

በሰሜን ማሊ ግዛት ፣ በማሊ ጦር እና በቱዋሬግ ተገንጣይ እና አማፂ ቡድኖች መካከል ግጭት ማገርሸቱን የጦር መኮንኖችና የአካባቢው ተመራጭ ባለስልጣናት ገለፁ።

በአውሮፓዊያኑ 2020 ስልጣን በኃይል ከያዙ በኃላ ፣ የአፍሪካዊት ሀገር የጦር መሪዎች ሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች ላይ ያላትን ሉዓላዊነት ማደስ ተቀዳሚ ተግባራቸው አድርገዋል ።ኪዳል የተባለው ቁልፍ ስፍራ የመጪ ጊዜያት የፍልሚያ ስፍራ ይሆናል የሚል ግምት አለ ።

አንድ ወታደራዊ መኮንን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት የማሊ ጦር የሀገሪቱን ብሄራዊ ግዛት ለማስከበር የምድር ጦር እንቅስቃሴ ቀጥሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአካባቢው ተመራጭ በበኩላቸው ጦርነቱ በኪዳል አካባቢ መቀጠሉን እና የአካባቢው ነዋሪዎች የሮኬቶች ድምፅ ስለመስማታቸው ተናግረዋል ።

የጦር አውሮፕላኖች እሁድ ወደ ኪዳል ሲበሩ መታየታቸውን ሌላ ባለስልጣን ተናግሯል።
ጦርነቱ የጀመረው ሀሙስ ዕለት የጦር ሰራዊቱ በኪዳል ክልል ሁሉንም የሽብርተኝነት ስጋቶች ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት ያቀዱ ስልታዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግ አውጆ ስፍራውን ዝግ ካደረገ በኃላ ነው ።

ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንታት ጀምሮ አኒፌስ የተባለው ቦታ ላይ ሰፍሮ የነበረው ጦር 110 ኪሎ ሜትሮች ርቃ ወደ ምትገኘው ኪዳል ግዛት ተንቀሳቅሷል ።

ወታደራዊ፣ፖለቲካዊ እና የአማፂያኑ ምንጮች ግጭቱን ዘግበዋል። ነገር ግን የጉዳት መጠን ወይም በጥቅም ላይ የዋሉ የውጊያ ስልቶችን በተመለከተ ወጣ ብሎ ከገለልተኛ ምንጮች ለማረጋጋጥ አልተቻለም ።

የኪዳል አማፅያን ከበርካታ ቀናት የአየር ድብደባ በኋላ ወታደራዊ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው እንደሚችል በመጠበቅ አርብ ዕለት የስልክ ግንኙነቶችን አቋርጠዋል።
ወደ አልጄሪያ በሚወስደው ጎዳና ላይ ቁልፍ ስፍራ በሆነው እና ታሪካዊ የዓመጽ መናኸሪያነቱ የሚታወቀው የኪዳል በረሃ አካባቢ ወደ 25,000 የሚጠጉ ሰዎች ይኖራሉ ። (ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው )

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG