በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት ለንደን ውስጥ ሰልፍ ወጡ



በጋዛ ላሉ ፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለንደን ውስጥ ሰልፍ ወጥተዋል ።
በጋዛ ላሉ ፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለንደን ውስጥ ሰልፍ ወጥተዋል ።

ከ300ሺ በላይ ፍልስጤማዊያንን የሚደግፉ ሰዎች በማዕከላዊ ለንደን በትናንትናው ዕለት ትዕይንተ - ህዝብ አድርገዋል ። በዚህ ወቅት በዋናው ሰልፍ ላይ ጥቃት ለማድረስ አድብተዋል ከተባሉ የተቀናቃኝ የቀኝ ጽንፍ ተቃውሞ ሰልፈኞች ጋር የተፈጠረ ግጭትን ተከትሎ ፖሊስ 120 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል ።

በፖሊስ እና የመጀመሪያው ዓለም ጦርነት መጠናቀቅን ለማሳብ በተሰየመው ቀን ላይ የተደረገውን ሰልፍ ለመቃወም በወጡ ሰዎች መካከል ግብግብ ተፈጥሯል ። ቀኑ ብሪታኒያ እና ሌሎች ሀገራት በጦርነቱ ያጧቸውን ዜጎቻቸውን የሚዘክሩበት ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሴኖታፕ ተብሎ በሚጠራው የጦርነቱ መታሰቢያ ስፍራ የታየውን ግጭት አውግዘዋል ። ታላቁን ሰላማዊ ሰልፍ በመቀላቀል ጸረ ሴማዊ ዝማሬዎችን እንዳሰሙ ፣ የአፍቃሪ -ሃማስ ምልክቶችን እና ልብሶችን እንዳነገቡ የከሰሷቸውን ፣ " የሀማስ አዛኞች " ሲሉ የጠሯቸውን በቃላት አጥቅተዋል ።

በእስራኤል እና ሀማስ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ትልቁ እንደሆነ የተነገረለት በጋዛ የተኩስ አቁም ይደረግ ዘንድ የጠየቀው ሰልፍ ከመካሄዱ አስቀድሞ ውጥረት ሰፍኗል ። የብሪታኒያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱላ ብሬቨርማን ሰልፎቹን " በደቦ የሚመሩ የጥላቻ ሰልፎች " ሲሉ ጠርተዋቸዋል ።

የለንደን ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ሰልፉን እንዲያግድ በሚኒስትሮች የቀረቡ ጥሪዎችን የከፋ ግጭት እንደሚኖር የሚያሳዩ ምልክቶች የሉም በሚል ሳይቀበል ቀርቷል ።

ፖሊስ ቅዳሜ አመሻሹን ላይ በሰጠው መግለጫ እስካሁን 126 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፣ ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ የቀኝ ክንፍ ተቃዋሚዎች ሲሆኑ፣ የእግር ኳስ ነውጠኞችን ጨምሮ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ቡድን የመጡ ሰዎች መሆናቸውን ፖሊስ አክሏል ።

ረዳት ኮሚሽነር ማት ትዊስት “ከቀኝ ክንፍ ተቃዋሚዎች በኩል በፖሊስ ላይ ዛሬ የደረሰው ከፍተኛ ጥቃት ያልተለመደ እና አሳሳቢ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል ። በፍተሻ ወቅት ቢላዋ እና በእጅ የሚጠለቁ የ ነሃስ መደብደቢያ አንጓዎች መገኘታቸውንም ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG