በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ የምድር ጦርነት እና የአየር ድብደባ ምሽቱን ቀጥሏል


ምስሉ የእስራኤል ጦር በፍልስጤም እስላማዊ ቡድን ሃማስ ላይ እያካሄደ ባለው የምድር ጦርነት ዘመቻ ወቅት የእስራኤል ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በጋዛ ሰርጥ በተጠንቀቅ ቆመው ያሳያል ።
ምስሉ የእስራኤል ጦር በፍልስጤም እስላማዊ ቡድን ሃማስ ላይ እያካሄደ ባለው የምድር ጦርነት ዘመቻ ወቅት የእስራኤል ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በጋዛ ሰርጥ በተጠንቀቅ ቆመው ያሳያል ።

በጋዛ የምድር ጦርነት እና የአየር ድብደባው በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት ፣ በጋዛ ከሚገኙት ሆስፒታሎች ሁሉ ትልቁ መሆኑ የተነገረለት አል-ሺፋ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ እንደተከበበ የሆስፒታሉ ኃላፊ መሀመድ አቡ ሳልሚያ ትናንት ቅዳሜ ምሽት ተናግረዋል።

የእስራኤል ጦር ቅዳሜ ዕለት ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ ካለበት አል-ሺፋ ሆስፒታል ሕፃናትን ለማስወጣት እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቋል።የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሪየር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ “የሚፈለገውን እርዳታ እናቀርባለን" ሲሉ በትናንትናው ዕለት አስታውቀዋል ።

ቅዳሜ በአል-ሺፋ ሁለት ሕፃናት ሲሞቱ ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ለኃይል ማመንጫ ማሽኖች የሚሆን ነዳጅ በማለቁ አደጋ ላይ ወድቀዋል።“የህክምና መሳሪያዎች ስራ አቁመዋል ። በተለይ በጽኑ ህክምና ስር የሚገኙ ህመምተኞች መሞት ጀምረዋል " ፣ ሲሉ የአል-ሺፋ ሆስፒታል ኃላፊ ሞሃመድ አቡ ሰልሚያ ፣ ፍንዳታ እና የጠመንጃ ተኩስ ድምጽ ከጀርባ ባጀበው የስልክ ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል ።

ሌሊቱን የቀጠለው ውጊያ ጨቅላ ሕፃናትን ከስፍራው ለማስወጣት የተያዘው ዕቅድ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ለጊዜው ግልጽ አልሆነም ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በሀማስ የጥቅምት 7 ጥቃት ወቅት የተወሰዱ ዜጎች የሚለቀቁበትን ሁኔታ ያላካተተ የተኩስ አቁም ጥሪን በጽኑ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል ።

ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን 4 የጋዛ ሆስፒታሎች በማያቋርጥ የቦምብ ድብደባ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግሯል ።ቡድኑ ፣ የአል-ሺፋ ሆስፒታል በተደጋጋሚ መደብደቡን ገልጾ ፣ የእናቶች እና የተመላላሽ ታካሚ ክፍሎች ከተደበደቡት መካከል መሆናቸው የብዙ ሰዎች ሞት እና ጉዳት ምክንያት እንደሆነ አስታወቋል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከባይደን አስተዳደር አቋም በተለየ መልኩ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት እንዳበቃ የፍልስጤም አስተዳደር ጋዛን ያስተዳድራል የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል።

"ልጆቻቸውን እስራኤልን እንዲጠሉ፣ እስራኤላውያንን እንዲገድሉ፣ የእስራኤልን መንግሥት እንዲያጠፉ የሚያስተምር ሲቪል አሰተዳደር አይኖርም።" ሲሉ ኔታንያሁ በቅዳሜው የጋዜጠኞች ማስገንዘቢያ መርሐ-ግብር ላይ ተናግረዋል ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጦርነቱ በኋላ የሚኖረውን አስተዳደር በተመለከተ እሮብ ዕለት ሁኔታዎችን በዝርዝር አስቀምጠዋል ።

"(የድህረ-ጦርነቱ አስተዳደር ) በፍልስጤም የሚመራ አስተዳደር እና በፍልስጤም አስተዳደር ስር ከዌስት ባንክ ጋር የተዋሃደውን ጋዛን ማካተት አለበት" ብለዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG