በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞሮኮ በርዕደ መሬት የወደመ ቅርሷን ለመገንባት 11.7 ቢሊዮን ዶላር መደበች


ባላፈው መስከረም በሞሮኮ በደረሰው ርዕደ መሬት ጉዳት ከደረሰባቸው ሥፍራዎች መካከል
ባላፈው መስከረም በሞሮኮ በደረሰው ርዕደ መሬት ጉዳት ከደረሰባቸው ሥፍራዎች መካከል

ባለፈው መስከረም በደረሰው ርዕደ መሬት ከ3ሺ ሰዎች በላይ የሞቱባት ሞሮኮ፣ በአደጋው የወደሙባትን ቅርስና ታሪካዊ ህንጻዎች መልሶ ለመገንባት ማቀዷ ተነገረ፡፡

ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ለማካሄድ ላሰበችው ግንባታ 11.7 ቢሊዮን ዶላር መመደቧ ተመልክቷል፡፡
የስነ ህንጻዎችና ቅርሶች ተመልሰው በሚገነቡበት ሁኔታ በባለሙያዎች መካከል ብርቱ ክርክር መከፈቱ ተሰምቷል፡፡

መልሶ ግንባታው ጥንታዊውን ባህልና ታሪክ ሳይለቅ የርዕደ መሬት አደጋዎችንም መቋቋም በሚችልበት ዘመናዊ መልክ እንዴት ሊሰራ ይችላል የሚለው በአገሪቱ ብርቱ ክርክር መፍጠሩን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ የተጎዱ ነዋሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡

ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው ቤተሰቦች 13,600 ዶላር ሲያገኙ በከፊል የወደመባቸው ደግሞ የ7,800 ዶላር ድጋፍ እንደሚያገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG