የ“ሁለት ሲደመር ሁለት ምክክር” በሚባል የሚታወቀው የአሜሪካ እና የህንድ የውጪ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የጋራ ውይይት በህንድ፣ ኒው ደሊ ላይ መካሄዱ ተሰምቷል።
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስትን፣ ከህንድ አቻዎቻቸው ከሆኑት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰብራማኒያም ጃይሻንካር እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ራጅናት ሲን ጋር ኒው ደሊ ላይ መክረዋል።
በዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ የፀጥታ ስጋቶች፣ በተለይም የስራኤል እና የሐማስ ጦርነት በተመለከተ እንደተወያዩ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
ህንድ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ፣ ‘ኳድ’ ተብሎ የሚጠራውና በቀጠናዊ ፀጥታ ላይ ያተኮረ ቡድን አባል አገራት ናቸው። የቻይናን እያየለ የመጣ ተጽእኖ ለመመከት ያለመ ቡድን እንደሆነ ተነግሯል።
በሌላ በኩል፣ ህንድ ከሩሲያ ጋር ያላትን የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ግንኙነት አጥብቃ ቀጥላለች፡፡ ይህም ሩሲያን ለማግለል የሚጥረውን የምዕራቡ ዓለም ያበሳጨ ጉዳይ ነው ተብሏል።
መድረክ / ፎረም