በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱስ አስያዥ መድሃኒት እና ሌሎችንም የያዙ ደብዳቤዎች ወደ ምርጫ ቢሮዎች ተልከው ተገኙ


የአደጋ ጊዜ እና የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች በሬንተን በሚገኘው የኪንግ አውራጃ ምርጫ ቢሮ
የአደጋ ጊዜ እና የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች በሬንተን በሚገኘው የኪንግ አውራጃ ምርጫ ቢሮ

ፈንትነል የተሰኘውን ሱስ የሚያሲዝ የውጋት መድሃኒት እና ሌሎችንም የያዙ ደብዳቤዎች በአሜሪካ በአምስት ግዛቶች ወስጥ ወደሚገኙ የምርጫ ቢሮዎች ማን እንደላካቸው ለማወቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

በካሊፎርኒያ፣ ጆርጂያ፣ ነቫዳ፣ ኦሪገን እና ዋሽንግተን ግዛቶች የሚገኙ የምርጫ ቢሮዎች ኢላማ እንደሆኑ የአሶስዬትድ ፕረስ ዜና ወኪል ዘገባ አመልክቷል።

“ምርጫውን አቁሙ” የሚል ጽሑፍ የያዘና፣ ፖርትላንድ ኦሪገን የሚገኝ ፖስታ ቤት ምልክት የተደረገበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ፒርስ አውራጃ የሚገኘው የታኮማ ዋሽንግተን ኦዲተር ቢሮ አስታውቋል።

በፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር ወደሚታይበት ጆርጂያ ግዛት በሚገኘው ፉልተን አውራጃ ምርጫ ቢሮ የተላከን ደብዳቤ በመንገድ ላይ ሳለ ለመያዝ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል። ፉልተን አውራጃ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ያለፈውን ምርጫ ውጤት ለመቀየር ሞክረዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው የምርጫ ክልል ነው።

ከተላኩት ደብዳቤዎች ውስጥ አራቱ ፈንትነል የተሰኘውን ሱስ የሚያሲዝ የውጋት መድሃኒት እንደያዙ፣ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) እና የአሜሪካ ፖስታ ምርመራ አገልግሎት አስታውቀዋል።

ሌሎች ደብዳቤዎች ተልከው እንደሁ ለመያዝ ሕግ አስከባሪዎች ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG