በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐዲያ ዞን መምህራን ሥራ በማቆማቸው መቶ ሺሕዎች ከትምህርት እንደራቁ ተገለጸ


በሐዲያ ዞን መምህራን ሥራ በማቆማቸው መቶ ሺሕዎች ከትምህርት እንደራቁ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

በሐዲያ ዞን መምህራን ሥራ በማቆማቸው መቶ ሺሕዎች ከትምህርት እንደራቁ ተገለጸ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን፣ ለወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ሥራ በማቆማቸው፣ እስከ አሁን፣ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ሒደት እንዳልተጀመረ፣ የተማሪዎች ወላጆች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ትምህርት ባልተጀመረባቸው በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ውጪ እንደኾኑ፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ አማርረዋል።

የዞኑ እና የክልሉ ባለሥልጣናት ስልካቸውን ስለማያነሡ፣ ምላሽ እና አስተያየታቸውን ለማካተት አልቻልንም።

ይኹን እንጂ፣ የሐዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ሓላፊ ዶክተር ክቢሞ ዴታሞ፣ ችግሩ መኖሩን አምነው፣ መንሥኤው የበጀት እጥረት ነው፤ ሲሉ፣ ከዚኽ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG