በሐዲያ ዞን መምህራን ሥራ በማቆማቸው መቶ ሺሕዎች ከትምህርት እንደራቁ ተገለጸ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን፣ ለወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ሥራ በማቆማቸው እስከ አሁን የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ሒደት እንዳልተጀመረ፣ ወላጆች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ትምህርት ባልተጀመረባቸው በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ውጪ እንደኾኑ፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ አማርረዋል። የዞኑ እና የክልሉ ባለሥልጣናት ስልካቸውን ስለማያነሡ፣ ምላሽ እና አስተያየታቸውን ለማካተት አልቻልንም።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025
በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025
የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025
አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025
ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች