በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዙ ሚኒስትር ፖሊሶች የፍልስጤም ደጋፊዎችን ይደግፋሉ ሲሉ ነቀፉ


የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፈኞች በማዕከላዊ ለንደን፣ ቻሪንግ አደባባይ ተቀምጠው የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ - ህዳር 4፣ 2023
የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፈኞች በማዕከላዊ ለንደን፣ ቻሪንግ አደባባይ ተቀምጠው የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ - ህዳር 4፣ 2023

የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱኤላ ብራቨርማን የሀገሪቱ ትልቁ የፖሊስ ኃይል ፍልስጤምን ለሚደግፉ ሰልፈኞች ከሌሎች ቡድኖች የተለየ ርህራሄ ያሳያሉ ሲሉ ከሰዋል።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰጡት ይህ አስተያየት በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት ሳቢያ በብሪታንያ የተቀሰቀሰውን ፖለቲካዊ ውዝግብ ማባባሱን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ብራቨርማን የለንደን እና ዙሪያዋ የፖሊስ ኃይል ህወገጥ ያሏቸውን “የፍልስጤም ደጋፊዎች ” ድርጊት ችላ ማለቱን በመክሰስ ያልተለመደ ጥቃት መሰንዘራቸው አነጋገሪ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሚኒስትሯ በጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲደረግ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎችን “የጥላቻ ሰልፈኞች” ሲሉ የገለጿቸው መሆኑም ብዙዎችን እንዳስቆጣ ተዘግቧል ።

ከአንድ ወር በላይ የሆነው የእስራኤል ሐማስ ጦርነት ከጀመረ ወዲህ ፍልስጤምን የሚደግፉ የተቃውሞ ሰልፎች በለንደን እና በሌሎች የእንግሊዝ ከተሞች በየሳምንቱ መጨረሻ ሲካሂዱ ቆይተዋል።

እንግሊዝ ውስጥ ብዙዎች የጦር ጉዳተኞችን በማሰብ እለቱን ያሳልፉበታል የተባለውን፣ የነገው ቅዳሜ ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅተዋል ያሏቸውን መሪዎች፣ የብሪታኒያ መንግሥት መተቸቱም ተዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG