በቅርቡ ሶማሊያ እና ኬንያ ውስጥ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የ40 ሰዎች ህይወት ማለፉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ። ሁኔታዎች ተባብሰው እየቀጠሉ መሆናቸውም ተመክቷል።
የኬንያ፣ ቀይ መስቀል እንደገለጸው በአደጋው ከ11,750 በላይ ቤተሰቦች የተጎዱ ሲሆን 6,000 የቤት እንስሳትም ተጠቅተዋል፡፡ የጎርፍ አደጋው በ65 የንግድ ተቋማትና እና በትምህርት ቤቶች ላይም ጉዳት አድርሷል።
የኬንያ መንግስት እንዳስታወቀው በህዳር ወር ከፍተኛ የዝናብ መጠን ሊጥል ስለሚችል ችግሩ እየተባባሰ እንደሚሄድ ይገመታል፣
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ተንታኞች ይህ ተጨማሪ መፈናቀል እና የኑሮ ውድመት እንደሚያስከትል ገልፀው፣ በኬንያ ከሚገኙ 47 አውርጃዎች ግማሽ ያህሉ ለአደጋ መጋለጣቸውን አስታውቀዋል።
በቅርቡ በኬንያ በደረሰው የጎርፍ አደጋም 15 ሰዎች መሞታቸውን በኬንያ የቀይ መስቀል ባለሥልጣን ፒተር ሙርጎር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም