በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳኑ ግጭት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተፈጠረ እንደኾነ የተመድ ባለሥልጣን አስታወቁ


ፋይል - እ.ኤ.አ. ሰኔ 16፣ 2023 የተነሳው ይህ ምስል፣ በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን፣ በምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ጀኒና ውስጥ ባሉ ቤቶች አቅራቢያ የወደቁ እና የተሸፈኑ አስከሬኖችን ያሳያል።
ፋይል - እ.ኤ.አ. ሰኔ 16፣ 2023 የተነሳው ይህ ምስል፣ በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን፣ በምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ጀኒና ውስጥ ባሉ ቤቶች አቅራቢያ የወደቁ እና የተሸፈኑ አስከሬኖችን ያሳያል።

በሱዳን እያየለ በመጣው ግጭት ምክንያት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እየተፈናቀሉና ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ እንደኾነ፣ አንድ ከፍተኛ የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን ባለሥልጣን አስታወቁ።

በሱዳን የነጭ አባይንና በደቡብ ሱዳን የሚገኙ አካባቢዎችን ጎብኝተው የተመለሱት፣ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር የውጭ ጉዳይ ሓላፊ ዶሚኒክ ሃይድ፤ የመጠለያ፣ የውኃ እና የምግብ እጥረት እንዳለ አመልክተዋል።

ተመድ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ የረድኤት ድርጅቶች በጋራ ቢንቀሳቀሱም፣ ካለው ፍላጎት አንጻር በቂ እንዳልኾነም ጠቁመዋል።

“መቆም በሚችል ግጭት ምክንያት፣ ስድስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ በሀገር ውስጥ እና በጉረቤት ሀገራት ተፈናቃይ ኾነዋል፤” ያሉት ሓላፊው፣ የተኩስ አቁም ተደርጎና የፖለቲካ መፍትሔ ተፈልጎ፣ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርገዋል።

“ይህ ኹኔታ ሊቀጥል አይችልም፤” ሲሉ፣ አሳስበዋል ዶሚኒክ ሃይድ።

የገንዘብ እጥረት፣ በሱዳንም ኾነ ከሱዳን ውጪ የሚደረገውን ሰብአዊ ሥራ እንዳስተጓጎለ፣ ሓላፊው አክለው ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG