በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትውልደ ሶማሊያ አሜሪካዊቷ ሴት በከንቲባነት ተመረጡ


ፋይል - ከፌስቡክ የምርጫ ቅስቀሳ ገጻቸው ላይ በተገኘው ፎቶ ላይ የሚታዩት ናዲያ መሀመድ፣ በሴንት ሉዊስ ፓርክ፣ ሚኖሶታ የተካሄደውን የምርጫ ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሱማሌ-አሜሪካዊ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል - ህዳር 7፣ 2023
ፋይል - ከፌስቡክ የምርጫ ቅስቀሳ ገጻቸው ላይ በተገኘው ፎቶ ላይ የሚታዩት ናዲያ መሀመድ፣ በሴንት ሉዊስ ፓርክ፣ ሚኖሶታ የተካሄደውን የምርጫ ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሱማሌ-አሜሪካዊ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል - ህዳር 7፣ 2023

በአሜሪካ፣ ትላንት በተደረገ የአካባቢ ምርጫ፣ በሜኒሶታ ግዛት የሚገኘው ሴይንት ሉዊስ የተባለች ከተማ፣ የመጀመሪያዋን ጥቁር፣ የመጀመሪያዋን ሴት እና የመጀመሪያዋን ሙስሊም፣ እንዲሁም የመጀመሪያዋን ትውልደ ሶማሊያ አሜሪካዊት፣ ከንቲባዋ አድርጋ መርጣለች።

የ27 ዓመቷ ናድያ ሞሐመድ፣ ዴል አንደርሰን የተባሉ የቀድሞ የባንክ ባለሞያ እና የተከታታይ ትምህርት መምህርን አሸንፈው ነው፣ የከንቲባውን ወንበር የያዙት፡፡

“እንደ ሶማሊ አሜሪካዊት፣ ሙስሊም፣ ስደተኛ እና ጥቁር፥ ምርጫውን በማሸነፌ ደስተኛ ነኝ። ለደገፉኝ ኹሉ አመስግናለኹ፤” ብለዋል ናዲያ፣ ከቪኦኤ ጋራ ባደረጉት ቆይታ።

ናድያ ሞሐመድ፣ በሕዝብ ምርጫ ከንቲባ የኾኑ የመጀመሪያዪቱ ትውልደ ሶማሊያ አሜሪካዊት ናቸው። ከሁለት ዓመት በፊት፣ በሜይን - ደቡብ ፖርትላንድ በተሰኘ ከተማ፣ ደካ ዳህላክ የተባሉ ትውልደ ሶማሊያ አሜሪካዊ ከንቲባ ኾነው ተመርጠዋል። እርሳቸው ግን ከንቲባነቱን ያገኙት፣ በከተማው ምክር ቤት ተመርጠው ነው።

ናዲያ ሞሐመድ፣ ከወላጆቻቸው ጋራ ወደ አሜሪካ ሲመጡ የ10 ዓመት አዳጊ ነበሩ። በ23 ዓመታቸው፣ 50ሺሕ ነዋሪ እንዳላት የምትገመተው ከተማ ምክር ቤት ተቀማጭ ኾነው፣ የ170 ዓመታት ዕድሜ ባለው አንጋፋ ምክር ቤት፣ የመጀመሪያዋ ወጣት አባል ኾነዋል።

ናዲያ በተጨማሪም፣ በከተማው የሰብአዊ አገልግሎት ቢሮም አገልግለዋል።

ባለፈው ዓመት በተደረገ የአካባቢ ምርጫ፣ 22 የሚደርሱ ትውልደ ሶማሊያ አሜሪካውያት ሴቶች አሸንፈው ወንበር ይዘዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG