በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች ግጭት ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግ ተጠየቀ


ለዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች ግጭት ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:09 0:00

ለዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች ግጭት ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግ ተጠየቀ

በዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጾኪያ ገምዛ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አርጡማ ፉርሲ አጎራባች ቀበሌዎች፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ በተቀሰቀሰ ግጭት፣ የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ፣ የአካል ጉዳት እንደደረሰ እና የደረሰ ሰብልም እንደወደመ ተገለጸ፡፡

ለግጭቱ መነሣት፣ ከሁለቱም አካባቢዎች የተለያዩ ምክንያቶች ሲሰጡ፣ ከአንጾኪያ ገምዛ በኩል፣ የደረሰ ሰብላችንን እንዳንሰበስብ ከአርጡማ ፉርሲ በኩል ጫና እና ጥቃት በመሰንዘሩ እንደኾነ፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የወረዳው ነዋሪ ይናገራሉ፡፡

በአንጻሩ፣ አንድ የአርጡማ ፉርሲ ነዋሪ የነበሩ የዕድሜ ባለጸጋ፣ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ውስጥ በመገደላቸው ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ፣ አስተያየታቸውን የሰጡ የአርጡማ ፉርሲ ነዋሪ ይገልጻሉ፡፡

ከእርሻ መሬት፣ ከውኃ እና ከግጦሽ ስፍራ ጋራ በተያያዘ፣ በሁለቱ ሕዝብ መካከል በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች ይቀሰቀሱ እንደነበር የተናገሩ አንድ አስተያየት ሰጪ ደግሞ፣ ለግጭቶቹ የብሔር ገጽታ በማላበስ ችግሩ እንዲባባሱ የሚሠሩ አሉ፤ ሲሉ ይተቻሉ፡፡ መንግሥትም፣ ከስብሰባ ባሻገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግ ይጠይቃሉ፡፡

መስፍን አራጌ እና ፀሐይ ዳምጠው ያጠናቀሩትን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ያቀርበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG