በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በክሳቸው ላይ ምስክርነት ለመስጠት ፍርድ ቤት ቀረቡ


ፋይል - የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በኒውዮርክ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የትራምፕ ድርጅት በተከሰሰበት የሲቪል ማጭበርበር ችሎት በተገኙበት ወቅት
ፋይል - የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በኒውዮርክ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የትራምፕ ድርጅት በተከሰሰበት የሲቪል ማጭበርበር ችሎት በተገኙበት ወቅት

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እና ኩባንያቸው፣ ማጭበርበር ፈጽመዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ዛሬ በኒው ዮርክ በሚገኝ ፍ/ቤት ቀርበዋል። ባለፈው ሳምንት ለሁለቱ ልጆቻቸው እንደቀረቡት የሰሉ ጥያቄዎች፣ ለቀድሞው ፕሬዝደንትም እንደሚቀርቡ የጠበቃል።

ትረምፕ እና ኩባንያቸው የነበራቸው የሂሳብ አያያዝ የተጭበረበረ ነው ሲሉ ዳኛው ቀድም ብለው አስታውቀዋል።

ትረምፕ፣ ከባንኮች እና ከሌሎችም ተቋማት የገንዘብ ብድር ለማግኘት ሲሉ፣ ሀብታቸውን እጅግ አጋነው በማቅረብ ማጭበርበር ፈጽመዋል በሚል ነበር የኒው ዮርክ ግዛት አቃቢያነ ሕግጋት ክስ ያቀረቡት፡፡ በዚህም 100 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝተዋል፣ ሀብታቸው ካለው ዋጋ 2 ቢሊዮን ዶላር ጨምረው አቅርበዋል ተብሏል። ትረምፕ ምንም ጥፋት እንዳላጠፉ ይገልጻሉ።

የኒው ዮርኳ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ልቲሺያ ጄምስ በትረምፕ ላይ 250 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣል ጠይቀዋል።

እንደሌሎቹ አራት ክሶች፣ ይኽኛው ክስ፣ ትረምፕን ለእስር የሚዳርግ አይሆንም ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG