በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን 1.6 ሚሊዮን ሕፃናት ረሃብ ሊገጥማቸው ይችላል ተባለ


የደቡብ ሱዳን ስደተኞች
የደቡብ ሱዳን ስደተኞች

በደቡብ ሱዳን፤ በየዓመቱ እየጨመረ በመጣው የጎርፍ አደጋ ምክንያት፣ በመጪው የፈረንጆች ዓመት 1.6 ሚሊዮን ሕፃነት ረሃብ ሊገጥማቸው እንደሚችል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዛሬ አስጠንቅቋል።

ፕሮግራሙ እንዳለው፣ በውሃ በተጥለቀለቀ አካባቢ ያሉ ሰዎች ምግብ ማግኘት አይችሉም። በተጨማሪም በጎርፍ ምክንያት እየጨመረ የመጣው የውሃ ወለድ በሽታም ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።

ግጭት፣ የተፍጥሮ አደጋ፣ የኢኮኖሚ ጉስቁልና እና የፖለቲካ ውጥንቅጥ የዓለም አዲሲቱን ሀገር ደቡብ ሱዳን ሲያብጣት ከርሟል።

በመጪው የፈረንጆች ዓመት ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት እንደሚገጥማቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG