የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽቴያ፣ በጋዛ የሚገኙ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ በሚመለከት ዌስት ባንክ በምትገኘው ራማላህ ከተማ በተደረገ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ማልቀሳቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር የእስራኤል የቅርስ ሚኒስትር አሚሃይ ኤሊያሁ “ጋዛ ላይ የኑክሌር ቦምብ መጣል አንድ አማራጭ ነው” ብለው የተናገሩትን በካቢኔው ስብሰባ ላይ አንስተው “ይህ ደም የጠማው እና ለመግደል ሲል ብቻ ሰውን የሚገድል” ሲሉ ተደምጠዋል።
የሚኒስትሩን አስተያየት ተከትሉ፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከካቢኔ ስብሰባ አግደዋቸዋል።
አስተያየታቸው የፈጠረውን ቁጣ ተከትሎ፣ “ዘይቤያዊ አነጋገር” መጠቀማቸው እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ የወንጅል ችሎት የመያዣ ትዕዛዝ እንዲያወጣም ሞሃመድ ሽቴያ ጠይቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሕፃነት ቀን ክብረ በዓልን ሰርዞ በምትኩ “በእስራኤል ገዳይ ማሽን” ብለው በጠቀሱት ምክንያት ት/ቤት መሄድ ያልቻሉትን ፍልስጤማውያን ሕፃናት ፎቶዎች እንዲያትም ጠይቀዋል።
በጦርነቱ የተገደሉትን ሲቪሎች ቁጥር በመመልከት፣ እስራኤል ያልተመጣጠነ ኃይል በመጠቀም ላይ ነች የሚል ነቀፌታ በመቅረብ ላይ ነው።
መድረክ / ፎረም