በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ


ፍልስጤማውያን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ዴር ባላ ተሰባስበው፣ በሹሃዳ አል-አቅሳ ሆስፒታል ላይ በእስራኤል በደረሰ የቦምብ ጥቃት ለተገደሉት ሰዎች ሀዘናቸውን ሲገልፁ።
ፍልስጤማውያን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ዴር ባላ ተሰባስበው፣ በሹሃዳ አል-አቅሳ ሆስፒታል ላይ በእስራኤል በደረሰ የቦምብ ጥቃት ለተገደሉት ሰዎች ሀዘናቸውን ሲገልፁ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲንዲ ማኬን በጋዛ የሚታየው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት በማየሉ እና ምግብም እያለቀ በመሆኑ፣ አስቸኳይ ርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አደረጉ።

በጋዛ እና በግብጽ መካከል በሚገኘው የራፋ መተላለፊያ ላይ ሆነው ጥሪ ያቀረቡት ሲንዲ ማኬን፣ “በጋዛ የሚገኙ እናቶች ዛሬን ልጆቻቸውን ስለመመገባቸው ወይም ነገን ስለማየታቸው እርግጠኞች አይደሉም” ሲሉ ተደምጠዋል። “በሚሊዮን ለሚቆጠሩ እና በቀውሱ ሕይወታቸው ለተመሳቀለ ሰዎች ርዳታ እንዲሰጥ አስቸኳይ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በግብጽ ጉብኝት ያደረጉት ሲንዲ ማኬን፣ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት አብደል ፋታሃ አል ሲሲ እና ከከፍተኛ ባለሥልጣኖች ጋር ተገናኝተዋል። በተጨማሪም በግብጽ የቀይ ጨረቃ እና በሌሎችም በራፋ የሚደረገውን የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትኩስ ዳቦ፣ ቴምር፣ እና የታሸገ ምግብ በማዳረስ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG