የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ኤጀንሲ በሱዳን በሁለቱ ተቀናቃኝ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ጦርነት እየተባባሰ በመምጣቱ፤ የዳርፉር ክልል የሰላማዊ ሰዎች የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እና የእርስ በርስ ግጭት እየጨመረ ነው ሲል አስታወቀ።
በዳርፉር በአራቱም ማዕዘናት በሱዳን ጦር ሃይሎች እና በፈጣን ደራሹ ደጋፊ ሃይሎች መካከል እንደገና የተቀሰቀሰው ግጭት “በደርዘን የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ገድሏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፣ የዜጎች ንብረት ወድሟል ወይም ጉዳት ደርሶበታል” ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።
በደቡብ ዳርፉር ኒያላ ባለፈው ሳምንት በትንሹ 17 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 35 ደግሞ ቆስለዋል። በተጨማሪም 17,500 ሰዎች ደግሞ ለደህንነታቸው ሲሉ ከቤት ንብረታቸው መሰደዳቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት OCHA ዘግቧል።
መድረክ / ፎረም