በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን በጆርዳን ስለ እስራኤል ሀማስ ጦርነት እና ስለ ሰብዓዊ ቀውስ ተወያዩ 


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጆርዳን
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጆርዳን

የዩናይትድስ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጆርዳን አማን ከአረብ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በዛሬው ዕለት ተገናኝተዋል። ብሊንከን የጆርዳን ባለስልጣናትን፣ የሳዑዲ አረቢያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የተባበሩት ዓረብ ኤመሬት፣ የግብጽ እና የኳታር ሚኒስትሮችን. እንዲሁም የፍልስጤም የነጻነት ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዋና ስራ አስፈጻሚን አግኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከባለስልጣናቱ ጋር በመሆን የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ እና በእስራኤል እና በሀማስ መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም እቅድ ሲያውጡ የቆዩ ሲሆን በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ከሊባኖስ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ ጋርም ተገናኝተዋል።

ብሊንከን በጆርዳን ጉብኝት ከማድረጋቸው በፊት የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ በሰጡት መግለጫ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ማቆም አለባት ያሉ ሲሆን እስራኤል በሰላማዊ ሰዎች ላይ በቦምብ በመደብደብ እና ከበባ በማድረግ የጦር ወንጀል እየፈፀመች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከስብሰባው በኋላ ብሊከን ከጋዜጠኞች ጋር ባደርጉት ቆይታ በጎርጎሮሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት በሀማስ የተፈጸመውን ዓይነት ጥቃት በድጋሚ እንዳይከሰት ለማድረግ እና “ለእስራኤል እና ለፍልስጤም ህዝቦች የተሻለ ወደፊት ለመገንባት” መወሰድ አለባቸው ያሏቸውን እርምጃዎች አጋርተዋል።

“እስራኤል ሀማስን ለመደምሰስ በምታደርገው ዘመቻ ላይ ግልጽ ሆነናል አተገባበሩም መሰረታዊ ጉዳይ ነው። መሰረታዊ የሆነው ደግሞ ህጋዊ እና ትክክለኛው ነገር ስለሆነ ነው። የሚያሳሰበን ይኼንን አለማድረግ ለሀማስ እና ለሌላ የሽብር ቡድን መዳፍ ላይ እንደንወድቅ ስለሚያደርግ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል እራሷን ለመከላከል የምታደርገውን መብቷን ታከብራለች ነገር ግን ደግሞ በጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲኖር ወታደራዊ እርምጃዎችን መውሰዷን እንደትገታ ትጠይቃለች ብለዋል።

በምላሹ ኔታንያሁ “በሙሉ ሀይላችን ወደፊት እንቀጥላለን፣ እስራኤልም የታጋቾቿን መለቀቅ ያላካተተ ጊዜያዊ እርቅ አትቀበልም” ብለዋል። በአሜሪካ አሸባሪ ተብሎ የተሰየመው ሀማስ በጥቃቱ 230 ሰዎችን ታግቶ 1,400 ሰዎችን ገድሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG