በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደገም እና ወረ ጃርሶ ወረዳዎች ግጭት 12 ሲቪሎች እንደተገደሉ ተገለጸ


 በደገም እና ወረ ጃርሶ ወረዳዎች ግጭት 12 ሲቪሎች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:01 0:00

በደገም እና ወረ ጃርሶ ወረዳዎች ግጭት 12 ሲቪሎች እንደተገደሉ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም እና ወረ ጃርሶ ወረዳዎች፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ 12 ሲቪሎች እንደተገደሉ፣ የወረዳው ነዋሪዎች በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ባነሡት ቅሬታ ላይ፣ ከጃርሶ እና ከደገም ወረዳዎች አስተዳዳር እና ጸጥታ፤ ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር እንዲሁም ከዞኑ ጸጥታ ጽሕፈት ቤት እና ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፣ በተጠቀሱት አካባቢዎች ታጣቂዎቻቸው ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋራ እየተዋጉ እንደኾነ አምነዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG