የኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የወሰዱ ተማሪዎቻቸውን፣ ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ከቻሉ አምስት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው የሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ት/ቤት ነው።
ትምህርት ቤቱ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መካከል፣ ከፍተኛው ውጤት የተመዘገበበት ሲኾን፣ በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን አስመዝግቧል።
እኒኽን ተደራራቢ መልካም ስኬቶች ያስመዘገበው የትምህርት ተቋም ግን፣ ጉዞው በፈታኝ ኹነቶች ተከቧል።
ሀብታሙ ሥዩም ከፈተናዎቹ ባሻገር ብርቱ ተማሪዎችን ማፍለቅ ስለቻለው ተቋም በጥቂቱ ይነግረናል።
መድረክ / ፎረም