በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲስ የእስራኤል-ሐማስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ጠየቁ


አቡነ ፍራንሲስ በቫቲካን የፀሎት ሥነ-ስርዓት ሲመሩ - ጥቅምት 18፣ 2016
አቡነ ፍራንሲስ በቫቲካን የፀሎት ሥነ-ስርዓት ሲመሩ - ጥቅምት 18፣ 2016

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ፣ በእስራኤል እና ሐማስ መካከል በሚካሄደው ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ጋዛ ውስጥ የተያዙ ታጋቾች እንዲለቀቁ እሁድ እለት ጠይቀዋል።

አቡነ ፍራንሲስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚያደርጉት ሳምንታዊ ቡራኬ ላይ "የጦር መሳሪያዎችን የማስቆም እድል እንዳለ ማንም ሊረሳ አይገባም" ሲሉም አሳስበዋል።

በቅድስት ሀገር ከቫቲካን ተወካዮች መካከል አንዱ የሆኑት ኢብራሂም ፋልታስ በቅርቡ በቴሌቭዥን ያቀረቡትን አቤቱታ በመጥቀስም "ተኩስ ይቁም" ብለዋል አቡነ ፍራንሲስ።

ሊቃነ ጳጳሱ ይህን ያሉት ሦስት ሳምንታት ባስቆጠረው ጦርነት፣ እስራኤል የሐማስ ቡድን ለማጥፋት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሁለተኛ ምዕራፍ ሲሉ የጠሩትን፣ የምድር ላይ ውጊያ ባወጀችበት ወቅት ነው።

አቡነ ፍራንሲስ "ተኩስ አቁም፣ ተኩስ ቁም እንላለን። ወንድሞች እና እህቶች፣ አቁሙ! ጦርነት ሁልጊዜ ሽንፈት ነው፣ ሁልጊዜም" ሲሉ ተማፅነዋል።

"በፍልስጤም እና በእስራኤል ያለውን አስከቸጋሪ ሁኔታ” በማመልከትም "በተለይ በጋዛ ለሰብዓዊ እርዳታ አስተማማኝ የሆነ ቦታ ይኑር፣ ታጋቾችም በአስቸኳይ ይለቀቁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡ የጋዛ ነዋሪዎች፣ የተባበሩት መንግስት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ መጋዘኖችን እና ማከፋፈያ ማዕከላትን ሰብረው በመግባት፣ ዱቄት እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ንብረቶችን መውሰዳቸውን ድርጅቱ እሁድ እለት አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG