በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በእሳላማዊ መንግስት ተደግፎ በተፈፀመ ጥቃት የኡጋንዳ ወታደሮች ተገደሉ


ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

በእስላማዊ መንግስት የሚደገፉ አማፂያን በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባደረሱት ጥቃት ሁለት የዩጋንዳ ወታደሮችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ንፁሃን ዜጎችን እና አንድ ተጠርጣሪ ጥቃት አድራሽ መገደላቸውን ባለስልጣናት አስታወቁ።

በሰሜን ኪቩ ግዛት የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት ባርቴሌሚ ካምባሌ እንዳስታወቁት፣ ከእስላማዊ መንግስት ጋር ቁርኝት ያላቸው ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በቤኒ ግዛት፣ ካሲንዲ የመኪና ማቆሚያ ላይ ባደረሱት ጥቃት፣ አንድ ኬንያዊ እና አንድ የኮንጎ ዜግነት ያለው የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ተገድለዋል። በስፍራው የተገኘው አምስተኛ አስክሬን የአጥቂው ሊሆን እንደሚችል መገመቱንም ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አስረድተዋል።

የእስላማዊው መንግስት ቡድን ቅዳሜ አሸሻሽ ላይ ቴሌግራም በተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ አማካኝነት ባስተላለፈው መግለጫ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎቹን በኮንጎ ከተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ለማስወጣት እ.አ.አ በ2021 የጋራ ጥቃት ቢያካሂዱም፣ አማፂያኑ አሁንም ጥቃቶችን ማድረስ ቀጥለዋል።

ታጣቂዎቹ ቤኒ በተሰኘው ግዛት ኦኢቻ ከተማ ውስጥ ከሰኞ ሌሊት እስከ ማክሰኞ አጥቢያ ባደረሱት ጥቃትም 26 ንፁሃን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን፣ ስፍራው ታጣቂዎቹ ለአመታት ተደጋጋሚ ጥቃት ያደረሱበት እና እስላማዊው መንግስት የመካከለኛው ምስራቅ ግዛቱ እንደሆነ የሚገልፀው ስፍራ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG