በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሂጃብ ህግ መተላለፍ የ16 ዓመቷ ኢራናዊት ህይወት አለፈ


አርሚታ ጌራቫንድ ጉዳት ከደረሰባት ባቡር ስትወጣ ( መስከረም 20/2016 ዓም)
አርሚታ ጌራቫንድ ጉዳት ከደረሰባት ባቡር ስትወጣ ( መስከረም 20/2016 ዓም)

ኢራን ውስጥ የሂጃብ ህግ ጥሰሻል በሚል እሁድ መስከረም 20/2016 ዓም ፖሊሶች ባደረሱባት ጉዳት ሆስፒታል የከረመችው የ16 ዓመቷ ኢራናዊት አርሚታ ጌራቫንድ ህይወት ማለፉን የኢራን ዜና አገልግሎት ዛሬ ቅዳሜ አስታውቋል፡፡

የአለባበስ ህግ በመጣስ በአግባቡ አልተሸፋፈንሽም የተባለቸው ጌራቫንድ ጉዳቱ የደረሰባት በባሩ ስትጓዝ በነበረበት ወቅት ከስነግምባር ፖሊሶች ጋር በተፈጠረ ግጭት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በወቅቱ በደረሰባት ጉዳት በመዘርር ሯስን ስታ የወደቀችው ጌራቫንድ እስከዛሬ ራሷን እንደሳተች ሆስፒታል መቆየቷ ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ባላፈው ዓመት መስከረም ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች ህይወቷ ያለፈው የ22 ዓመቷ ማሻ አሚኒ፣ ኢራን ውስጥ ለዓመታት ታይቶ ለማይታወቅ፣ ወራት ለቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ሆና መቆየቷ ይታወሳል፡፡

በ1972 ዓም በዓለማውያን እና ምዕራባውያን ይደገፉ የነበሩት ሻህ ከስልጣን ከተባረሩ ወዲህ ኢራን ውስጥ ሴቶች ፀጉራቸውን እንዲሸፍኑ፣ ዘለግና ጥብቅብቅ ያላሉ ልብሶችን እንዲለብሱ በህግ እንደሚገደዱ በሮይተርስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG