በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሽንግተንን በመጎብኘት ላይ ናቸው


የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዋሽንግተን ዲሲ
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዋሽንግተን ዲሲ

የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ምናልባትም ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የአሜሪካ ባልሥልታናትን ለማነጋገር ዋሽንግተን ይገኛሉ።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ለሶስት ቀናት የሚያደርጉት ጉብኝት፣ በፕሬዝደንት ባይደን እና በፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ መካከል ጉባኤ እንዲደረግ በማመቻቸት፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የተረጋጋ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።

ዋንግ ዪ ትናንት ሐሙስ ከቀጥር በኋላ ዋሽንግተን እንደገቡ፣ ከአሜሪካው አቻቸው አንተኒ ብሊንከን ጋር ተገናኝተዋል።

ግንኙነቱን ወደ ተሻለ ቦታ በማድረስና ጤናማ እና ዘላቂ ልማት እንዲኖር ለማስቻል፣ ቻይና መግባባት እና ትብብር እንዲፈጠር እንደምትሻ ዋንግ ዪ ስብሰባው በዝግ ከመካሄዱ በፊት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ቻይና፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት መደግፏ እና በእስራኤል እና ሐማስ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት በተመለከተ በአንጻራዊ ጸጥታን መምረጧ፣ አሜሪካንን ያበሳጨ ጉዳይ እንደሆነ ተዘግቧል።

“ቻይና ያላትን ማንኛውንም ተጽእኖ የማድረግ አቅሟን ተጠቅማ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ጸጥታ እንዲሰፍን ማድረግ አለባት” ሲሉ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG