በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ይታያል ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት ገለጸ


በኤርትራ፤ በማኅበራዊ መብት፣ በተለይም በትምህርት እና በጤና እንዲሁም በሴቶች መብትና በዘላቂ ልማት ግቦች ረገድ መሻሻል መታየቱን በመልካም እንደሚቀበለው ያስታወቀው የአውሮፓ ኅብረት፣ በሀገሪቱ የሚታየው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግን እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ኤርትራ፣ የተመድ የሰብ ዓዊ መብት ም/ቤት ባስቀመጠው የሰብዓዊ መብት ግምገማ አሰራር እና በአፍሪካ የአቻ የእርስ በእርስ ግምገማ ላይ ተሳታፊ መሆኗ የሰብዓዊ መብትን በተመለከተ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ውይይት እንዲካሄድ በር የሚከፍት ነው ያለው ኅብረቱ፣ የሰብዓዊ መብትን በተመለከተ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል።

በርካታ ኤርትራውያን በዘፈቀደ ይታሠራሉ፣ ሌሎች ደግሞ ደብዛቸው ይጠፋል ያለው የአውሮፓ ኅብረት፣ የተያዙትን እና የጠፉትን ሰዎች በተመለከተ ኤርትራ መልስ እንድትሰጥ ጥሪ አድርጓል።

በዘፈቀደ ማሠር፣ ሰዎች በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲሰወሩ ማድረግ፣ የሃስብ ነጻነት እና የመሰብሰብ እንዲሁም የመደራጀት ነጻነትን መገደብ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ተግባር መሆኑን ኅብረቱ አስታውቋል።

ኤርትራ 13 የሚሆኑ ጅቡቲያውያን የጦር ምርኮኞች ያሉብትን እንድታሳውቅም ኅብረቱ ጠይቋል።

የኤርትራ መንግስት የግዜ ገደብ የሌለው ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎትን እና ሕጻናትን በግዳጅ መመልመል እንዲያቆም ኅብረቱ ጠይቋል።

ኅብረቱ በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ መሠረት፣ ኤርትራ የቀራትን ጦር ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ፣ እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ተፈጽመዋል የተባሉ ጥሰቶች እንዲመረመሩ በድጋሚ ጥሪ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG