በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የተከሠተው የወባ በሽታ፣ በአካባቢው የሰላም ዕጦት ምክንያት እንደተባባሰ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሓላፊ ዶክተር ተስፋዬ ከበበው አስታወቁ።
የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት እና ለመቆጣጠር፣ የጤና ቢሮው፣ ከደንበር ውጪ የሕክምና አገልግሎት ከሚሰጡ የጤና ባለሞያዎች እና ከሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋራ ንግግር እንደጀመረ፣ ምክትል ሓላፊው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
የዞኖቹ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በየቀኑ በወባ በሽታ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደኾነ አመልክተዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም