በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በጣልቃ ገብነት ወቀሱ


የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በጣልቃ ገብነት ወቀሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:03 0:00

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በጣልቃ ገብነት ወቀሱ

በትግራይ ቴሌቪዥን የሚሠሩ ጋዜጠኞች፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ ጣልቃ እየገባ ፍትሕን እያጓደለብን ነው፤ ሲሉ፣ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ላይ ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡

ጋዜጠኞቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የፌዴራሉ መንግሥት፣ በ2013 ዓ.ም. በትግራይ ክልል አቋቁሞት በነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር፣ “የሥራ ምድብ ተሰጥቷችኹ በብዙኀን መገናኛው ሠርታችኋል፤” በሚል፣ 40 የሚደርሱ ሠራተኞች ከሥራ ደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሠሩ ተደርገዋል፡፡

በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያቀረቡት 19ኙበፍርድ ቤት ወደ ሥራ ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንደታዘዛላቸው የገለጹት ጋዜጠኞቹ፣ “ውሳኔው ግን አልተከበረም፤” ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እና ምላሽ እንዲሰጠን የአሜሪካ ድምፅ የጠየቀው የትግራይ ቴሌቪዥን አመራር፣ “ሒደቱ ገና ያልተጠናቀቀ ነው፤” ሲል፣ ማብራርያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

በተመሳሳይ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG