በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ


የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:06 0:00

የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በአንዳንድ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት እና ጋዜጠኞች ላይ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የኅትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈጸሙ የገለጸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት፣ ሥራቸውን ለማከናወን እየተቸገሩ እንደኾነ አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ፣ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ስላወጣው መግለጫ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ኃይሉ፣ የእገዳ ድርጊቱ ተፈጽሞባቸዋል ያሏቸው ሁለት የብዙኀን መገናኛዎች፣ የዕለት ከዕለት ሥራዎቻቸው እንደተስተጓጎለ አመልክተዋል፡፡

“በጸጥታ ኀይሎች፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ተፈጽሟል ያለው ይኸው ድርጊት እንዳሳሰበው” የጠቀሰው የምክር ቤቱ መግለጫ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅም ውስጥ ቢኾን፣ በጋዜጠኞች እና በብዙኀን መገናኛ ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት፣ ሕጋዊነትን የተከተለ ሊኾን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG