በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል በዜጎች ላይ የሚፈጸመው እገታ በመባባሱ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እየለቀቁ መኾኑን ተናገሩ


በኦሮሚያ ክልል በዜጎች ላይ የሚፈጸመው እገታ በመባባሱ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እየለቀቁ መኾኑን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:21 0:00

በኦሮሚያ ክልል በዜጎች ላይ የሚፈጸመው እገታ በመባባሱ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እየለቀቁ መኾኑን ተናገሩ

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ፣ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች፣ በዐሥሮች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች እንደታገቱ፣ ከእገታው የተለቀቁ ሰዎች፣ የታጋች ቤተሰቦች እና የመንግሥት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አጋቾቹ፣ የያዟቸውን ሰዎች ለመልቀቅ፣ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቁ የተናገሩ ሲኾን፣ ከድርጊቱ መደጋገም የተነሣ ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው የገለጹ ነዋሪዎችም፣ ቀዬአቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ አመልክተዋል፡፡

እገታ ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች በአንዳቸው እንደተወለዱ የገለጹና ስለኹኔታው የሚያውቁ አስተያየት ሰጪ፣ ሰሞኑን፣ ስምንት አርሶ አደሮች በነፍስ ወከፍ እስከ 300ሺሕ ብር የማስለቀቂያ ቤዛ እንደከፈሉ ተናግረዋል፡፡ ከእገታው የተለቀቁ አንድ ግለሰብ ደግሞ፣ ነጻ ለመውጣት፣ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋራ፣ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለናል፤ ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን፣ ለእገታው ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ እንደኾኑ የሚገልጹት አቶ ኦዳ ተርቢ በበኩላቸው፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG