በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የቦልቲሞር ካምፓስ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር ተመሠረተ


በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የቦልቲሞር ካምፓስ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር ተመሠረተ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:48 0:00

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የቦልቲሞር ካምፓስ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር ተመሠረተ 

ሳሮን ክብከባው እና ዕድላዊት ጋረደው፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ቦልቲሞር ካምፓስ፣ የኢትዮ-ኤርትራውያን ተማሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንደቅደም ተከተላቸው ናቸው። ማኅበሩ፣ ከመቶ በላይ ንቁ አባላት አሉት።

ሁለቱ ጓደኛሞች፣ ባለፈው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ፣ የዩኒቨርሲቲ የኢትዮ-ኤርትራ ማኅበራት በሚያዘጋጇቸው መሰናዶዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ከዩኒቨርሲቲያቸው አንዳንዴም ካሉበት ግዛት ራቅ ብለው መጓዝና ብዙ ኪሎ ሜትሮችን መንዳት ነበረባቸው።

አሁን ግን፣ በራሳቸው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ፣ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር እንዳቋቋሙ፣ ጓደኛሞቹ ሳሮንና ዕድላዊት ይናገራሉ።

በአሁን ሰዓት ማኅበራቸው፣ ከመቶ በላይ አባላት ያፈራ ሲኾን፣ በአዕምሮ ጤና፣ በባህል ትስስር እና ማኅበረሰቡን በሚደግፉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ላይ፣ በበጎ ፈቃድ እና ገቢ በማሰባሰብ ይሳተፋል።

ኤደን ገረመው፣ ከተማሪ ማኅበሩ መሥራቾች ጋራ ቆይታ አድርጋ ያሰናዳችው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG