በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ተማሪዎች የነፃ የትምሕርት ዕድል የሚያመቻቸው ተቋም  


ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ተማሪዎች የነፃ የትምሕርት ዕድል የሚያመቻቸው ተቋም  
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ተማሪዎች የነፃ የትምሕርት ዕድል የሚያመቻቸው ተቋም  

የአፍሪካ ዳያስፖራ የኮሌጅ ተደራሽነት ፕሮግራም፣ ከአውሮፓውያኑ 2016 አንሥቶ፣ ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ ለተውጣጡ እና በቁጥር ለተወሰኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም ኤርትራውያን ተማሪዎች፤ የነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ሲያግዝ ቆይቷል፡፡

ድርጅቱ፣ ዓመቱን ሙሉ በሚሰጠው ድጋፍ፣ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች፡- የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጽሑፎችን ማዘጋጀት፣ የአደባባይ ንግግር እና ሌሎች የባህል ተሞክሮዎችን ያስተምራል። ድርጅቱ በቅርቡ፣ ስሙንና ተደራሽነቱን በመቀየር፣ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለመጡ ቤተሰቦችም አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የድርጅቱ መሥራች አቶ ማቴዎስ መስፍን፣ እኤአ በ2022-2023 የትምህርት ዘመን መጨረሻ፣ 80 ተማሪዎችን ማገዛቸውንና እያንዳንዱ ተማሪ በአማካይ 175ሺሕ ዶላር የስኮላርሺፕ ድጋፍ እንደተቀበሉ ገልጿል። በተቋሙ ድጋፍ የተደረገላቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች፣ እንደ ሃርቫርድ፣ ዬል፣ ፕሪስተን፣ ኮርኔል፣ ኮሎምቢያ... ወደመሳሰሉ ታዋቂ ዩኒቨርስቲዎች የመግባት ዕድሉን አግኝተዋል። ኤደን ገረመው የተቋሙን መሥራች እና ሁለት በዬል እና በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የነፃ የትምህርት ዕድል ያገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን አነጋግራ ትምሕርት ፕሮግራም ያሰናዳችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG