በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ500 በላይ የሾኔ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው


ከ500 በላይ የሾኔ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

ከ500 በላይ የሾኔ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው

በሐዲያ ዞን ሾኔ ከተማ፣ ላለፉት ሦስት ወራት የተቋረጠባቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የገለጹ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች፣ በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ፡፡

በጊዜያዊ ውል የተቀጠሩትን ጨምሮ ከ500 በላይ የሆስፒታሉ ጠቅላላ ሠራተኞች እንደተስማሙበት በጠቀሱት በዚኹ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት፣ ለ600ሺሕ ገደማ ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ፣ ሥራ ከአቆመ ዛሬ ሰባተኛ ቀን እንደኾነው፣ ሠራተኞች እና ታካሚዎች ተናግረዋል፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ተድላ አካሉ፣ ሆስፒታል ሥራ ማቆሙን አረጋግጠው፣ በተለይ የድንገተኛ ክፍል አገልግሎቱ ከተቋረጠ፣ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን እንዳስቆጠረ ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ተሰማም፣ ሆስፒታሉ ሥራ ማቆሙን ባይክዱም፣ መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከሐዲያ ዞን ጤና መምሪያ አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት፣ ለሓላፊው አቶ ታከለ ኦልባሞ ስልክ ስንደውልላቸው፣ ስብሰባ ላይ እንደኾኑ ጠቅሰው፣ “እዚያው ሆስፒታሉን ጠይቁ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተውናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG