በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤኳዶር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባለሀብቱ አሸነፉ


በኤኳዶር በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ባለሀብቱ ዳንኤል ኖቦዋ አሸናፊ ኾነዋል።
በኤኳዶር በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ባለሀብቱ ዳንኤል ኖቦዋ አሸናፊ ኾነዋል።

በኤኳዶር በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ባለሀብቱ ዳንኤል ኖቦዋ አሸናፊ ኾነዋል። በአገሪቱ ታሪክም፣ በዕድሜ ወጣቱ ፕሬዚዳንት ኾነዋል።

እስከ አሁን ከተጣለው ድምፅ 96 በመቶው ድምፅ ሲቆጠር፣ ኖቦዋ 52ነጥብ2 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ፣ ተፎካካሪያቸውና ግራ ዘመሙ ጠበቃ ሉዊሳ ጎንዛለዝ ደግሞ 47ነጥብ8 በመቶ አግኝተዋል። ጎንዛለዝ፣ በስደት ያሉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ራፋኤል ኮሪያ የቅርብ ሰው እንደኾኑ፣ ተነግሯል።

በሙዝ ንግድ ሀብት ያካበት ቤተሰብ ወራሽ እንደኾኑ የተነገረው ዳንኤል ኖቦዋ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ኢኮኖሚዋ የተንገዳገደውንና ዜጎቿ በገፍ ለቀው የውጡባትን ሀገር የማስተካከል ሥራ ይጠብቃቸዋል፤ ተብሏል። ወንጀል፣ ግድያ እና ዝርፊያም በአገሪቱ ተስፋፍቷል።

ዳንኤል ኖቦዋ፤ እንደራሴዎች ክስ ሊመሠርቱባቸው ሲዘጋጁ፣ መንግሥታቸውን አፍርሰው ሥልጣናቸውን የለቀቁት የፕሬዚዳንት ጊሌርሞ ላሶን፣ ቀሪ ሁለት ዓመት የፕሬዚዳንትነትን ዘመን እንደሚሸፍኑ ተገልጿል።

በኤኳዶር የምርጫ ዘመቻ፣ ጉቦንና የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኖችን ለመፋለም የተነሡት ተፎካካሪው ፈርናንዶ ቢያቢሴንሲዮ፣ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG