በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ሕዝብ በጦርነት የደረሰበት ኀዘን እንዳይደገም የፖለቲካ አመራሩ ራሱን እንዲፈትሽ ፕሬዚዳንቱ አሳሰቡ


የትግራይ ሕዝብ በጦርነት የደረሰበት ኀዘን እንዳይደገም የፖለቲካ አመራሩ ራሱን እንዲፈትሽ ፕሬዚዳንቱ አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00

የትግራይ ሕዝብ በጦርነት የደረሰበት ኀዘን እንዳይደገም የፖለቲካ አመራሩ ራሱን እንዲፈትሽ ፕሬዚዳንቱ አሳሰቡ

በትግራይ ክልል በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሕይወታቸው ያለፈ የቀድሞ ተዋጊዎች፣ ላለፉት ሦስት ቀናት በኀዘንና በጸሎት ተዘክረዋል፡፡

ለሦስት ቀናት የታወጀውን የኀዘን ቀን ተከትሎ፣ በመቐለ ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ኾነው ሰንብተዋል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ “ለምን ወደዚኽ ሥቃይ እና መከራ ገባን ብለን፣ እኛ እንደ አመራር ራሳችንን ልንፈትሽ፣ ንስሓም ልንገባ ያስፈልጋል፤” ሲሉ በዝክር መርሐ ግብሩ ወቅት ተናግረዋል።

በመታሰቢያ ቀናቱ በክልሉ የታየው ከባድ ኀዘን እንዳይመጣ፣ ብዙ ተማጽኖ ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ “ዛሬም ግን ካለፉት የጦርነት ታሪኮች ባለመማር፣ ከብዙ አካባቢዎች የምንሰማው የእልቂት ዜና ኾኖ ያውከናል፤” ሲሉ፣ በአገሪቱ የቀጠሉ የትጥቅ ግጭቶችን አሳሳቢነት አመልክተዋል።

በክልሉ የታወጀውን የኀዘን ቀን ተከትሎ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ኣብርሃም በላይ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዲሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኀኖም፣ ለክልሉ ሕዝብ የማጽናኛ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG