በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰሜን ኮሪያን ይጎበኛሉ


የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ

ሰሜን ኮሪያ፤ በዩክሬን ጦርነት ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ለሩሲያ አቅርባለች ስትል አሜሪካ ክስ ባሰማች በቀናት ውስጥ፣ የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ሰሜን ኮሪያ እንደሚያቀኑ በመነገር ላይ ነው።

ሰርጌይ ላቭሮቭ ረቡዕ እና ሐሙስ ፒዮንግያን እንደሚጎበኙ ያስታወቀው የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስለ ጉዞው ዓላማ እና ከየትኛው ባለሥልጣን ጋር እንደሚገናኙ ያለው የለም።

የጦር መሣሪያ የያዙ ከአንድ ሺሕ በላይ ኮንቴይነሮች ከሰሜን ኮሪያ ወደ ሩሲያ ተልኳል ሲል ዋይት ሃውስ ባለፈው ዓርብ አስታውቆ ነበር። ይህንንም የሚያሳዩ ያላቸውን ፎቶግራፎች ይፋ አድርጎ ነበር።

ባለፈው ወር ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የተገናኙት እና የሩሲያን ወታደራዊ ተቋማት የጎበኙት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን፣ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የመሳሪያ ክምችቷ ለተመናመነው ሩሲያ ተጨማሪ መሣሪያ ለመለገስ ሳያስቡ አይቀርም የሚል ግምት አሳድሯል።

በምትኩም፤ ሰሜን ኮሪያ፣ የወታደራዊ እና የኑክሌር ፕሮግራሟን ለማሳለጥ ዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ከሩሲያ ትሻለች ሲሉ የዋይት ሃውስ ብሔራዊ የጸጥታ ም/ቤት ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG