በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪፐብሊካኖች ጂም ጆርዳንን ለአፈጉባኤነት መረጡ


ለአፈጉባኤነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባል ጂም ጆርዳን
ለአፈጉባኤነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባል ጂም ጆርዳን

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔን ለመምረጥ ትርምስ ውስጥ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሪፐብሊካን አባላት ትናንት ዓርብ ምሽት ባደረጉት የሶስተኛ ቀን ሙከራ 124 ለ 81 በሆነ ድምጽ የወግ አጥባቂ ተወካይ ጂም ጆርዳንን መርጠዋል፡፡

ጆርዳን አፈ ጉባኤ ሆነው ለመመረጥ የሚያበቃቸውን የሙሉ ምክር ቤቱን አብላጫ ድምጽ በሚቀጥለው ሳምንት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ በማይኖሩ ጊዜ በሀገሪቱ ሶስተኛው ተተኪ የሚያደርጋቸውን ከፍተኛ የአፈ ጉባኤነት ሥልጣን ለማግኘት ጆርዳን ለሳቸው ድምጽ ያልሰጡትን ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት በማሳመን ብርቱ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል፡፡

እረፍት የወጡት የዴሞክራት እና ሪፐብሊካን አባላት በሪፐብሊካኖች ለተመረጡት ጆርዳን ወይም ለዴሞክራቱ እጩ ሀኪም ጀፍሪ ድምጽ ለመስጠት የፊታችን ሰኞ ወደ ዋሽንግተን ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምክር ቤቱ አብላጫውን ወንበር በያዙት የሪፐብሊካን አባላት መካከል ስምምነት ባለመኖሩ ምክር ቤቱ እስካሁን አፈጉባኤ የለውም፡፡

በዚህ ሳቢያም ወደ እስራኤልም ሆነ ዩክሬን የሚላኩ እርዳታዎችን የሚያጸድቁ ህጎችን ማውጣት አለመቻሉ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG