በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሣሪያዎችን በመስጠት ተከሰሰች


ሰሜን ኮሪያ ወደ ሩሲያ የጦር መሣሪያዎችን የምታስተላልፍበትን አቅጣጫ የሚያሳያ ምስል
ሰሜን ኮሪያ ወደ ሩሲያ የጦር መሣሪያዎችን የምታስተላልፍበትን አቅጣጫ የሚያሳያ ምስል

ዋይት ሐውስ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ለሩሲያ የጦር መሣሪያ ታቀብላለች ሲል ትናንት ዓርብ ክስ አሰምቷል፡፡

ትናንት የተለቀቁት የሳተላይት ምስሎች ከሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት የወጡ የጦር መሣሪያና ጥይቶች መኖራቸውን እንደሚያረጋጡ ዋይት ሐውስ አስታውቋል፡፡

መሣሪያዎቹ ከሰሜን ኮሪያ የሩሲያን ባንዲራ ባውለበለቡ መርከቦች ከተጫኑ በኋላ በደቡባዊ የሩሲያ ድንበር በኩል በባቡር ተጭነው የተጓጓዙ መሆኑን ዋይት ሐውስ አመልክቷል፡፡

መሣሪያዎቹ የተጓጓዙት እኤአ ከመስከረም 7 ጥቅምት 1 መሆናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡

የብሄራዊ የደህንነት አማካሪው ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ “ሰሜን ኮሪያ የዩክሪን ከተሞች ለማጥቃት፣ ዩክሬናውያንን ለመግደልና ህገወጡን የሩሲያ ጦርነት ለማራዘም ለሩሲያ ወታደራዊ መሳሪያዎች መስጠቷን እናወግዛለን” ሲሉ ትናትን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ከርቢ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በሰጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ “ከ1000 ኮንቴይነር በላይ ወታደራዊ መሣሪያዎችና ጥይቶችን” ለሩሲያ መስጠቷን ገልጸዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የዩናይትድ ስቴትስ የተዋጊ አውሮፕላኖች ተሻካሚ ቡድን ደቡብ ኮሪያ መድረሱ አስመልክቶ “ያፈጠጠ ወታደራዊ ትንኮሳ ነው” በማለት የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት ለመሰዘነር ማቀዷን ያሳያል" ስትል ትናንት ዓርብ ብርቱ ነቅፋ አሰምታለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሣሪያን አስቀድሞ መጠቀምን ከሚከለክለው ስምምነት ውጭ ቀድማ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችልም አስጠንቅቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG