በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል የጋዛ ድብደባ ቀጥሏል


እስራኤል የአየር ድብደባ፣ ጋዛ፣ እአአ ዕሮብ 11/2023
እስራኤል የአየር ድብደባ፣ ጋዛ፣ እአአ ዕሮብ 11/2023

የታደሰ

እስራኤል፣ በጋዛ ሰርጥ 200 የሚደርሱ ዒላማዎችን ዛሬ ለሊት እንደመታች አስታውቃለች፡፡ ሠራዊቷንም በጋዛ ድንበር አካባቢ በማከማቸት ላይ እንደኾነችና የምድር ጥቃት ሊደረግ እንደሚችል እየተጠበቀ ይገኛል።

በጋዛ 900 የሚደርሱ ሰዎች እንደሞቱና 4ሺሕ600 ደግሞ እንደተጎዱ፣ የፍልስጥኤም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ሐማስ፣ ባለፈው ቅዳሜ ባደረሰው ጥቃት፣ በእስራኤል ወገን የተገደሉት ብዙኀን ሲቪልያን የኾኑ ሰዎች ቁጥር 1ሺሕ200 መድረሱንና 2ሺሕ700 ደግሞ እንደተጎዱ ተነግሯል።

ቁጥሩ ያሻቀበው ተጨማሪ አስከሬኖች በመገኘታቸው እንጂ፣ እስራኤል ውስጥ እየተካሔደ ያለ ውጊያ በመኖሩ እንዳልኾነ፣ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። ሐማስ ጥሶ የገባውን ድንበር መዝጋቷንና የአካባቢ ጥበቃዋን ማጠናከሯን፣ እስራኤል ገልጻለች፡፡

በጋዛ ሰርጥ፣ 263 ሺሕ ሰዎች መኖሪያ ቤታቸውን ጥለው መውጣታቸውንና ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG