በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል እና የሐማስ ግጭት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚኖረው ተጠቆመ


የእስራኤል እና የሐማስ ግጭት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚኖረው ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:28 0:00

የእስራኤል እና የሐማስ ግጭት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚኖረው ተጠቆመ

በእስራኤል እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የእድገት ዕቅድ ስኬት ላይ፣ ተጨማሪ ፈተና ሊኾን እንደሚችል፣ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ጠቆሙ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሞያዎቹ፣ ሳይጠበቅ የተፋፋመውና ዓለም አቀፋዊ ተጽእኖዎችን የሚያስከትለው የሁለቱ ኀይሎች ግጭት፣ የነዳጅ ዋጋን በማናር እና የሰብአዊ ርዳታ ድርጅቶችን ትኩረት በማስቀየር፣ በሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ከትላንቱ የፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ንግግር፣ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረን የጠየቅናቸው፣ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ ኾነው እየሠሩ ያሉት ዶክተር ዘሪሁን ጌታቸው፣ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት፣ መንግሥት ሀገራዊ ሰላምን በማረጋገጥ ምርትንና ምርታማነትን ለማሳደግ መሥራት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሰውአለ አባተ በበኩላቸው፣ በፕሬዚዳንቷ ንግግር የተነሡ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ጥሩ ቢኾኑም፣ ለመተግበር የሚያስችል አስቻይ ኹኔታ አሁን በሃገሪቱ አለመኖሩን አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG