በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ በደቡብ ምዕራብ የሚገኙ 400 ወታደሮቿን በማስወጣት ከኒጀር መልቀቅ እንደምትጀር የጁንታ መሪው አስታወቀ


ፋይል - የኒጀር ሴቶች ወታደራዊ አገዛዙን ደግፈው በፈረንሳይ ጦር ዋና መስሪያ ቤት ፊት ባደረጉት ሰልፍ አንዲት ሴት "ከአሁን በኃላ ፈረንሳይን አንፈልግም" የሚል መፈክር ይዛ ትታያለች - ነሐሴ 30፣ 2023
ፋይል - የኒጀር ሴቶች ወታደራዊ አገዛዙን ደግፈው በፈረንሳይ ጦር ዋና መስሪያ ቤት ፊት ባደረጉት ሰልፍ አንዲት ሴት "ከአሁን በኃላ ፈረንሳይን አንፈልግም" የሚል መፈክር ይዛ ትታያለች - ነሐሴ 30፣ 2023

በደቡብ ምዕራብ ኒጀር፣ ኡዋላም የተሰኘች ከተማ ውስጥ የሚገኙት 400 የፈንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው መውጣት እንደሚጀምሩ የኒጀር ወታደራዊ መሪ አስታውቋል። ይህም ፈረንሳይ በግጭት በሚታመሰው የሳህል ቀጠና የነበራት ተጽእኖ ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንደሚያደርስ ተገልጿል።

የፈረንሳይ ጦር ከኒጀር መውጣቱ፣ በሐምሌ ወር ስልጣን የተቆጣጠሩት የጦር ኃይሎች ቁልፍ ጥያቄ ነበር።

ፈረንሣይ መጀመሪያ ላይ የጁንታውን ሕጋዊነት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆን ተቃውማ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማርኮን ከኒጀር ጋር ያላቸውን ወታደራዊ ትብብር ለማቆም እና 1ሺህ 500 የሚሆኑ የፈረንሳይ ወታደሮችን ለማስወጣት ውሳኔ አሳልፈዋል። ይህም ምዕራባውያን አማፂያንን ለመመከት በሚያደርጉት ጥረት ላይ ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሯል።

ጁንታው አክሎ፣ አብዛኞቹ የፈንሳይ ወታደሮች የሰፈሩበት፣ በዋና ከተማዋ ኒያሜይ የሚገኘው የአየር ጦር ሰፈርም በአመቱ መጨረሻ እንደሚፈርስ አስታውቋል።

ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ፣ በቀድሞ የአፍሪካ ቅኝ ግዛቶቿ ላይ ያልት ተጽእኖ እየቀነሰባት የሄደችው ፈረንሳይ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። ሆኖም ሐሙስ እለት ከፓሪስ የወጣው መግለጫ፣ ከኒጀር የመውጣቱ ሂደት በዚህ ሳምንት እንደሚጀመር እና በአመቱ መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ፣ ዝርዝር ሁኔታዎችን ሳይገልፅ አመልክቷል።

እያደገ የሄደውን ፀረ-ፈረንሳይ ስሜት ተከትሎ፣ በማሊ፣ በቡርኪናፋሶ እና በኒጀር መፈንቅለ መንግስት ያካሄዱት መሪዎች ከፈረንሳይ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያቋረጡ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG